አተገባበሩና መመሪያው
በብላክ-ፋየር ገጣሚው / ፓትሪክ ስቲቭ በድሊ የሚሸጡ የዲጂታልም ሆነ የፊዚካል ምርቶች በአዕምሯዊ ንብረትነት የተመዘገቡ ሲሆኑ የህግ ከለላ የተሰጣቸው ናቸው። የተሸጡት የሙዚቃዎች እና/ወይም የምስል ስራዎች የቅጂ-መብት(ኮፒራይት) ባለቤቶች ለሶስተኛ-ወገን ተጠቃሚዎች አሳልፈው ሲሰጡ በዚህ ውል መሠረት ሲሆን ይህን ውል በእናንተ ላይ ማስተግበር ይችላሉ፣ እንዲሁም በዚህ ውል መሰረት ማንኛውንም መብት መሰረዝ ይችላሉ፣ ይኸውም የግዴታ ገደብንም ያካትታል። ለእርስዎ የሚሰጡ ሁሉም ፈቃዶች በብቸኝነት የሚሰጧችሁ አይደሉም። ይህን ውል መሠረት በማድረግ እያንዳንዷን ነገር ተከታትለን ማስፈፀም ባንችል እንኳ መብታችንን እንዳናስፈፅም የሚያግደን ነገር አይኖርም። በዚህ ውል ውስጥ ከተካተቱት ውስጥ አንዳቸው እንኳ ቢሰረዙ፣ ቢወገዱ፣ ወይም በማንኛውም ምክንያት የማይተገበሩ ቢሆኑ፤ ያ የውል ይዘት ብቻውን ተነጥሎ የማይካተት ሲሆን በሌሎቹ የውል ወይም የሁኔታዎችን የይዘት ተግባራዊነት ወይም አግባብነት ላይ ተፅዕኖ አያሳርፍም። ከዚህ ውል እና/ወይም ሁኔታዎች ጋር በተያያዘ የሚነሱ ክርክሮች ወይም ጥያቄዎች በፍርድ-ቤት የመፈታት ግዴታ አለባቸው። በዚህ ድረ-ገፅ ላይ ምንም አይነት ግዢ ስትፈፅሙ ወይም በነፃ የምታገኟቸውን ምርቶች ስታወርዱ በእነዚህ ውሎች ተስማምታችሁ ነው። ከእኛ በገዛችሁት ወይም ከድረገፁ ካገኛችሁት ሶፍትዌር ከአጠቃቀማችሁ ጋር በተያያዘም ሆነ አጠቃቀም ከአለማወቅ የተነሳ ለሚደርስባችሁ ጉዳት በምንም አይነት መልኩ ተጠያቂ አይደለንም፤ እንዲሁም በይዘቱ ላይ ሊገኝ የሚችል፤ ሌሎችን የሚያጠቃ፣ ጨዋነት-የጎደለው፣ ወይም ለማያስደስት ነገር እኛ ተጠያቂ አይደለንም። ህክምናዎቹ የታለመላቸውን ግብ ሳይመቱ ቢቀሩ እንኳ እነዚህ ገደቦች በእናንተ ላይ የሚጣሉ ይሆናል። ብላክ-ፋየር ገጣሚው / ፓትሪክ ስቲቭ በድሊ በዚህ የተገለፁ ወይም የተጨመሩ ዋስትናዎችን በሙሉ አይቀበልም፣ ይህም ማለት፣ ለሽያጭ መደራደሪያነት የሚሰጥ ዋስትናን ጨምሮ፣ በአንድ ውሱን ቁመና፣ ስያሜ፣ እንዲሁም የባለቤትነት መብት ላይ የሚሰጡትን የሚያካትት ሲሆን፤ በእነዚህ ብቻ ይገደባል ማለት ግን አይደለም። ለምንም አይነት ውጤት ዋስትና አንሰጥም። በመዘዝም ሆነ በአጋጣሚ ለሚደርስ ጉዳት ወይም ለሚደርስ የትርፍ ማጣት ወይም የገቢ ማጣት ብላክ-ፋየር ገጣሚው / ፓትሪክ ስቲቭ በድሊ በምንም አይነት ሁኔታ ተጠያቂ አይሆንም።
Add your own footer in your admin control panel: System > Edit Footers